አገልግሎቶችን በራስዎ ቋንቋ ያግኙ

የቋንቋእገዛ የማግኘት መብትዎ

በራስዎ ቋንቋ የስቴት ፕሮግራሞችን፣ ጥቅማጥቅሞችን እና አገልግሎቶችን ያለ ምንም ክፍያ የማግኘት መብት አለዎት። ከልጆች፣ የወጣቶች እና ቤተሰቦች ዲፓርትመንት (DCYF) ጋር ሲገናኙ የቃል ተርጓሚ አገልግሎቶችን እንዲሁም ሰነዶች ወደ እርስዎ በሚመርጡት ቋንቋ የተተረጎሙ ማግኘት ይችላሉ። 

በቋንቋ አገልግሎቶች ረገድ እገዛ ለማግኘት፣ ለቋንቋ ተደራሽነት በ dcyf.languageaccess@dcyf.wa.gov ኢሜይል ይላኩ።

በልጆችላይ የሚፈጸም ጥቃት ወይም ችላ ማለትን ሪፖርት ያድርጉ

1-866-363-4276

በልጆች ላይ የሚደረስ ጥቃትን፣ ችላ ማለትን፣ ፈቃድ የሌለው የህጻናት እንክብካቤን እና ከህጻናት እንክብካቤ ጋር የተያያዙ ስጋቶችን ሪፖርት ለማድረግ በዚህ ስልክ ቁጥር ይደውሉ። የሚናገሩትን ቋንቋ የሚረዳ ተርጓሚ ማግኘት ይችላሉ።

Constituent Relations

ConstRelations@dcyf.wa.gov | 1-800-723-4831 | 360-902-8060

Constituent Relations ከዚህ በታች ለተዘረዘሩት ጉዳዮች ፍትሃዊ እና ጨዋነት የተሞላበት ቅሬታ ፈቺ ሂደት ያቀርባል፡-

  • የልጆች ጥበቃ እና የልጆች ደህንነት ጉዳዮች
  • የአሳዳጊ ቤተሰብ እና የህጻናት እንክብካቤ ፈቃድ አሰጣጥ
  • የህጻናት እንክብካቤ ፕሮግራሞች
  • የወጣቶች ማገገሚያ አገልግሎቶች

የ DCYF ማዕከላዊ የመቀበያ መስመር

1-866-363-4276

DCYF ለቤተሰቦች የሚሆኑ በርካታ አገልግሎቶችና ድጋፎች አሉት። ከእነዚህ መካከል አንዳንዶቹን ከክፍያ ነፃ በሆነው የስልክ መስመር በመደወል ማግኘት ይችላሉ፤ እንዲሁም የእርስዎን ቋንቋ ከሚናገር አስተርጓሚ ጋር መገናኘት ይችላሉ። 

አገልግሎቶችየሚከተሉትን ያካትታሉ፡-

  1. ከ0 እስከ 3 ዓመት ለሆኑ ህጻናት የቀድሞ ጣልቃ-ገብነት አገልግሎቶች።
  2. በመላ ግዛቱ የሚሰጡ የድጋፍ፣ የትምህርት እና የአመራር ፕሮግራሞች።
  3. ደህንነቱ የተጠበቀ እና ተመጣጣኝ ዋጋ ያለው የህጻናት እንክብካቤ የማግኘት እርዳታ
  4. የቤት ጉብኝት፣ የማህበረሰብ ተደራሽነት እና የገንዘብ ድጋፍ።
  5. ወደ አካባቢያዊ ማህበራዊ አገልግሎቶች እና ድጋፍ የሚደረጉ ሪፈራሎች።

ነጻ ወይም ዝቅተኛ ዋጋ ያለው የህጻናት እንክብካቤ

1-844-626-8687

በWashington state’s Child Care Subsidy program አማካኝነት በነጻ ወይም በዝቅተኛ ዋጋ የህጻናት እንክብካቤ አገልግሎት ለማግኘት ብቁ ሊሆኑ ይችላሉ። ጥያቄዎች ካሉዎት ወይም ለማመልከት እርዳታ ከፈለጉ፣ በስልክ በተለያዩ ቋንቋዎች ድጋፍ ማግኘት ይቻላል። 

የአድልዎ ቅሬታ ማቅረብ

ለሚከተሉትጉዳዮች አድልዎ ሪፖርት ለማድረግ እባክዎ የ DCYF Service Access and Civil Rights Complaint Form ቅጽ ይሙሉ፦

  • የአካል ጉዳተኞች የሆኑ አሜሪካውያንን የሚመለከት ሕግ (Americans with Disabilities Act) 
  • የተሃድሶ ሕግ አንቀጽ 504 (Section 504 of the Rehabilitation Act) 
  • የሲቪል መብቶች ሕግ ርዕስ VI (Title VI of the Civil Rights Act) 
  • የቋንቋ አገልግሎቶች ማግኘት አለመቻል (Lack of Access to Language Services)
  • የተጠበቀ ክፍል (Protected Class)